“ ፈረንጆች፣ በውቀት ይሁን በስ ህተት በየትኛው መሆኑን እግዜር ይወቀው የሚጽፉት ሆነ የሚያስተምሩት፣ ፈረንጅን እና የፈረንጅ የሆነውን ሁሉ የሚያስወድ ድ፣ የሚያስደንቅ፣ የሚያስመኝ፣ ሌሎችንና የ ሌሎች የሆነውን፣ እኛንና የኛ የሆነውን ጭምር አዋርዶ፣ አጎሳቅሎ የሚያሳይና የሚያስንቅ፣ የሚያስጠላ፣ የሚያስጸይፍ ነው።
ታዲያ እንግዲህ፣ ከህጻንነታቸው ጀምረው እንዲያ ያለውን ትምርት ብቻ በትምርት ቤት እየተማሩ የሚያድጉ ልጆች፣ እንዲያ ያለው ትምርት እውነት አለመሆኑን የሚያስረዳ ማረሚያ ማስተባበያ፣ ማስተሀቀሪያ በመስጠት ፈንታ፣ በሱ ለላቁ ሽልማት እየሰጠን በሱ እንዲመሩ እያደፋፈርን የምናስድጋቸው ልጆች በጠቅላላው የራሳቸው የሆነውን የሚንቁ የሚጠሉ፣ በጠቅላላው የፈረንጅ የሆነውን ሁሉ የሚወዱ፣ የሚያደንቁና የሚመኙ መሆናቸው የማይቀር ነው።” ( ሀዲስ
አለማየሁ፣የልም ዣት)
“ የቆየ ልማድ የቆየ በመሆኑ ሁሉ አይወድቅም፤ ወይም ሁሉ አይያዝም። መልካሙና ጠቃሚው ይያዛል የሚሻሻለው ይሻሻላል ሊሻሻል የማይችለው ይወድቃል። ነገር ግን የሚወድቀው ክፉ ልማድ ከስራ ይወገዳል እንጂ ከታሪክ ጸሃፊዎች መጽሀፍና ከደራሲዎች ድርሰት ሊወገድ አይገባውም። ያለዚያ በየጊዜው የሚደረገው የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚክ ወይም የአስተዳደርና የማህበራዊ ኑሮ መሻሻል ከምን ተነስቶ እምን እንደደረሰ ሊታወቅ አይችልም።” ( ሀዲስ
አለማየሁ፣ፍቅር እስከ መቃብር)
“ በኔ አስተያይት ዛሬ ኢትዮጵያ በጣም የሚያስፈልጋት ኢኮኖሚዋን አፋጥኖ አልምቶ በጠቅላላ የህዝብዋን የኑሮ ደረጃ ማሻሻልና ያስተዳድርዋንም ሆነ የፍርድ ስራትዋን ለዘመናዊ ኑሮ እንዲስማማና ልማቱን እንዲረዳ ማድረግ ነው እንጂ የምዕራብን ወይም የምስራቅን ያስተዳድር ስራት እንዲሁ እንዳለ ተውሶ መልበስ ምስራቅን፣ ወይም ምዕራብን ሊያደርጋት አ ይችልም። ስለዚህ ያቀረብነው አሳብ ከምዕራብና ከምስራቅ የመንግስት ስሪቶች ለ ኢትዮጵያ ዘመናዊ አስተዳድርና ልማትዋን ለማፋጠን ይረዳሉ ተብሎ የሚታመንባቸው አሳቦች ተዋጥተው ያሉበት፣ በዚያ ላይ ከ ኢትዮጵያ ታሪክና ባህል ጋር የሚስማሙ አዳዲስ አሳቦች የተጨመሩበት፣ አይነተኛ አላማው ባሥር ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያን በፖለቲካ፣ በ ኢኮኖሚክና በማኀበራዊ ኑሮ አሁን ካለችበት ዝቅተኛ ቦታ በኃይል ገፍቶ ወደፊት ሊያራምዳት ይችላል ብለን የምናምንበት ነው።” ( ሀዲስ
አለማየሁ፣ኢትዮጵያ ምን አይነት አስተዳደር ያስፈልጋታል)
***********************************************************
ምንጭ:-- ሀዲስ አዲስ
No comments:
Post a Comment