እያንዳንዱ ሰው በቀን 2 ሊትር ምራቅ ያመርታል
በየደቂቃው ከ30ሺ - 40ሺ የቆዳ ሴሎች ይሞታሉ
ዓይኖቻችን በየዕለቱ 15ሺ ያህል ጊዜ ይርገበገባሉ
ከተፀነስንበት ሴኮንድ ጀምሮ፣ በሕይወትና በጤንነት የምንንቀሳቀሰው ቅንጣት ታህል ስህተት ሳይፈፅሙ ተግባራቸውን ስለሚፈፅሙ ነው፡፡
እስቲ ጥቂቱን እንይ፡፡ 20ሺህ ያህል ሀሳቦች በአንጎላችን ውስጥ ምን ያህል የነርቭ
ሴሎች እንዳሉ ያውቃሉ? እጅግ በርካታ ናቸው-እስቲ ይገምቱ፡፡ በአንድ ሴኮንድ ውስጥ በአማካይ ከአምስት እስከ 50
ጊዜ እርስ በርስ መልእክት ይለዋወጣሉ፡፡ የነርቭ ሴሎች የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች በቀን ከ10ሺ ኪ.ሜ በላይ
ይጓዛሉ፡፡ ከአዲስ አበባ አስመራ ድረስ አምስት ጊዜ እንደመመላለስ ነው፡፡ የነርቭ ሴሎቹ ቁጥር ከመቶ ቢሊዮን በላይ
ነው፤ የፀጉር ያህል ውፍረት የላቸውም፡፡ በመሃላቸው ያለው ርቀትም እንደዚያው ኢምንት ነው፡፡ ነገር ግን
ከብዛታቸውና በየሴኮንዱ ከሚለዋወጡት የመልእክት ብዛት የተነሳ ተዓምር ይፈጥራሉ፡፡ አንድ ነገር አይተው ወዲያውኑ
“ይሄ ውሻ ነው፣ እንዳይነክሰኝ!” “ብርቱካን ነው፣ ይጣፍጣል” “ሰው ነው፤ ዝነኛው ሯጭነቱ ይደነቃል” “አንበሳ
ነው፣ የጀግንነት ምሳሌ ተደርጎ ይቆጠራል” … ለማለት የሚችሉት በዚህ ፍጥነት ነው፡፡ በእነዚህ ነርቮች ነው
እንግዲህ በቀን፣ 20ሺህ ያህል ጊዜ የምናስበው።
እንደ በረዶ እንዳንቀዘቅዝ፣ እንደ ውሃ እንዳንፈላ
የሰውነታችን
“አውቶማቲክ” እንቅስቃሴዎችንና ሂደቶችን የሚቆጣጣረው hypothalamus የተባለው የአንጎል ክፍል ነው፡፡
የሰውነታችን የሙቀትና የቅዝቃዜ መጠን ከልክ እንዳያልፍም ይቆጣጠራል፡፡ በአንዳች ውጫዊ ወይም ውስጣዊ ምክንያት
የግማሽ ዲግሪ ሴንቲግሬድ ለውጥ ከተፈጠረ፤ ሰውነታችን ሕይወት አድን የሙቀት መጠን ማስተካከያ ያከናውናል፡፡
የሰውነታችን
ሙቀት በጣም ከፍ ሲል፣ በቆዳችን ውስጥ ያሉ የደም ስሮች ይሰፉና ሙቀት ያስወጣሉ፡፡ ቅዝቃዜ ሲከሰት ደግሞ የደም
ስሮች ጠበብ ይላሉ፤ ላብ አመንጪ ዕጢዎችም ይዘጋሉ፡፡ ቅዝቃዜው ሲበረታማ ሰውነታችን ሙቀት ለመፍጠር መንቀጥቀጥ
ይጀምራል፡፡
የልብ ምት
የትም ሆነ የት ቢሆኑ፣ ሲራመዱም ሆነ
ሲያንቀላፉ፣ ልብ በአንድ ደቂቃ ከ60 እስከ መቶ ጊዜ ይመታል፡፡ በአማካይ ልብዎ በቀን መቶ ሺህ ጊዜ ይመታል፡፡
በዚህ ስሌት ስድሳ ዓመት አማካይ ዕድሜ ላይ የደረሰ ሰው ከ2 ቢሊዮን ጊዜ በላይ የመታ ልብ ይኖረዋል፡፡
በሰውነታችን
ውስጥ የሚገኙ የደም ስሮች ብዛትና ርዝመት ጉድ ያሰኛል፡፡ ከጫፍ ጫፍ የተቀጣጠሉ 160 ሺህ ኪ.ሜ ያህል
ይረዝማሉ፡፡ የደም ማጣሪያ ባይኖር ኖሮ፣ ሰውነታችን ምን ያህል የደም መጠን እንደሚያስፈልገው ያውቃሉ? በቀን
5,720 ሊትር! በሌላ አነጋገር እንደ ሳንባ፣ ጉበትና ኩላሊት የመሳሰሉ የደም ማጣሪያ የሰውነት ክፍሎች በቀን ወደ
6ሺ ሊትር ገደማ ደም የማጣራት አቅም አላቸው ማለት ነው፡፡
ሳይፈልጉ በቀን 25ሺህ ጊዜ መተንፈስ
አልመውና አቅደው
25ሺህ ያህል ጊዜ ልተንፍስ ካሉ፣ ሌላ ነገር በፍፁም አይሰሩም፤ እንቅልፍም አይተኙም፡፡ ቀንና ሌት ስራዎ መተንፈስ
ብቻ ይሆናል፡፡ ስለዚህ አንጎላችን የመተንፈስ ልምድን አውቶማቲክ ስላደረግልን ምስጋና ይግባው፡፡ ለመሆኑ በየጊዜው
አየር ወደ ውስጥ የምንስበውና የምናስወጣው (የምንተነፍሰው) ለምንድነው?
የሰው ልጅ ፍጡራን በእያንዳንዷ
ደቂቃ ከ200 እስከ 300 ግራም ገደማ ኦክስጅን ያስፈልገናል፡፡ ይህንን የማያቋርጥ የአየር ፍሰት ለማስተናገድ
ሳንባችን ውስጥ 300 ሚሊየን ያህል ለዓይን የማይታዩ alveali የተባሉ የአየር ከረጢቶች ተዘጋጅተው ይጠብቃሉ፡፡
የተቃጠለ አየር (ካርቦንዳይ ኦክሳይድ) ከደማችን ያስወግዳሉ፤ ኦክስጅንን ተቀብለው ለደማችን ያስረክባሉ፡፡
የዓይን ጡንቻዎች
አንድ ነገር ላይ እንድናተኩር የሚረዱን የዓይናችን ጡንቻዎች በቀን 100ሺህ ጊዜ
ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ይህም ከ80ኪ.ሜ ጉዞ ጋር እኩል ይሆናል፡፡ ዓይኖቻችን በየእለቱ 15ሺህ ያህል ጊዜ ይርገበገባሉ፡፤
ለምን እንደሆነ ያውቃሉ? ዓይንን ከአደጋ ለመከላከል፣ ቆሻሻ ለማስወገድና ዓይንን ለማርጠብ ነው፡፡ ዓይናችንን
ስንጨፍንና ስንከፍት ያመለጠንን መረጃ አንጐላችን ስለሚያሟላልን መጨፈናችን እንኳ በፍፁም ትዝ አይለንም፡፡
ሁለት ሊትር ምራቅ
ሰውነታችን በቀን የሚያመነጨው ምራቅ ከጥቂት ማንኪያ የማይበልጥ ሊመስለን ይችላል፡፡
እያንዳንዱ ሰው በቀን ሁለት ሊትር ምራቅ ያመርታል፡፡ “አቤት! ምን ሊጠቅም?” ሊሉ ይችላሉ፡፡ ያለ ምራቅ አንድ
ነገር መቅመስ፣ ምግብ መዋጥም ሆነ ቃላት መፍጠር አንችልም፡፡ በዚያ ላይ፣ ምራቅ ከፍተኛ የጀርም ጠላትና የምርቀዛ
(የኢንፌክሽን) መከላከያ ነው፡፡ ስለዚህ፣ እንስሳት ቁስላቸውን ሲልሱ ማየት አያስደንቅም፡፡
በሴኮንድ 3 ሚሊዮን ቀይ የደም ሴል
በየደቂቃው፣ ከኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር በእጥፍ የሚበልጡ ቀይ የደም
ሴሎች በሰውነታችን ውስጥ ይፈጠራሉ፡፡ የዚያኑ ያህልም ይሞታሉ፡፡ በቀን 260 ቢሊዮን ያህል ቀይ የደም ሴሎች
እናመርታለን ማለት ነው፡፡ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ኦክስጂን ለሁሉም የሰውነታችን ሴሎች የሚዳረሰው በቀይ የደም
ሴሎች ነው፡፡ አንድ ጠብታ ደም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቀይ የደም ሴሎች ሲኖሩት፣ ቀዩን ቀለም የሚያገኙት ሄሞግሎቢን
ከተሰኘው ፕሮቲን ነው፡፡
መብላትና መጠጣት ጥበብ ነው
ምግብ መዋጥና ፈሳሽ መጠጣት ቀላል ጥበብ እንዳይመስላችሁ፡፡ ህፃናት ሲቸገሩ ካላየን በቀር በእግር ቆሞ መራመድ ቀላል ይመስለን የለ? ጥበብ ነው፡፡ ምግብ መዋጥና ፈሳሽ መጠጣትም እንደዚያው ነው፡፡
የአዋዋጥን
ጥበብ ለማድነቅ ከፈለጉ፣ ሕፃን ልጅ በማንኪያ ስታጐርሱት ምን እንደሚያደርግ ተመልከቱ፡፡ በምላሱ ምግቡን ወደ ውጭ
ገፍቶ ያስወጣዋል፡፡ ለምን መሰላችሁ? ወደ አየር መተላለፊያ እንዳይገባ የሚያደርግ የአዋዋጥ ስልት ገና በሚገባ
ስላልተካነበት ነው፡፡
ምንጊዜም ምግብ ሲበሉም ሆነ ፈሳሽ ሲጠጡ፣ ከአፍ ጀርባ፣ ምግቡም ሆነ መጠጡ ወደ አየር
ቧንቧ እንዳይሄድ ዘግተው የሚከላከሉ አስገራሚ ሕይወት አዳኝ የሰውነት ክፍሎች አሉ፡፡ የሚበሉትንና የሚጠጡትን
ነገር ለመዋጥ ሲዘጋጁ፣ Soft Palate የተሰኘው አካል ይመጣና ወደ አፍንጫ የሚወስደውን መተላለፊያ ይዘጋል፡፡
ወደ ሳንባችን እንዳይገባ ደግሞ Epiglottis ይከላከላል፡፡
የሆድ ውስጣዊ ግድግዳ ራሱን ያድሳል
የሆድ ግድግዳ በየሳምንቱ እንደሚታደስ ያውቃሉ? ሆዳችን፣
ሃይድሮክሎሪክ አሲድ የተባለ ኃይለኛ አሲድ የሚውልበትና የሚያድርበት ቤት ነው፡፡ አሲዱ ምግብን ሰባብሮ ይበልጥ
እንዲብላላ ይረዳል” አሲዱ ከባድ በመሆኑ፣ ብረት የማቅለጥ አቅም አለው፡፡ የጨጓራ ጡንቻ በአሲድ እንዳይጎዳም ነው፤
የሆዳችን ግድግዳ በአራት ወይም በአምስት ቀን ራሱን የሚያድሰው፡፡
አጥንት
እንደ ብረት ጠንካራ፤ እንደ አሉሚኒየም ቀላል የሆነው አጥንታችን፣ ሕይወት አልባ ምሰሶ ነገር
ወይም ድጋፍ አይደለም፡፡ የራሱ የደም ስርና ነርቭ ያለው ሕያው አካል ነው፡፡ በየጊዜው ሳያቋርጥ ራሱን ያድሳል፡፡
የአዋቂ አጥንት በየዓመቱ 10 በመቶ ያህል ራሱን ይተካል፡፡
የምድር ወገብን በእግር መዞር
ጤነኛ ሰው በአማካይ በየቀኑ ከ8 እስከ 10ሺህ እርምጃዎች ይጓዛል፡፡ በ70 ዓመት የምድርን ወገብ አራት ጊዜ እንደዞረ ይቆጠራል፡፡
50 ሚሊዮን ያህል የቆዳ ሴሎች ይሞታሉ
በየደቂቃው ከ30 እስከ 40ሺህ የቆዳ ሴሎች ይሞታሉ፡፡ ቆዳዎ፣ በየቀኑ 50 ሚሊዮን ያህል የሞቱ ሴሎችን ያስወግዳል ማለት ነው፡፡
ከሰውነት
ክፍሎች ሁሉ ትልቁ አካል ቆዳ ነው ሲባል ሰምተው ይሆናል፡፡ ምክንያቱም በርካታ ጠቃሚ ነገሮች ስለሚሠራ ነው፡፡ 5
ሴንቲ ሜትር በ5 ሳንቲ ሜትር ስፋት ያለው ቆዳ፤ 650 የላብ ዕጢዎች፣ 9 ሜትር ያህል የደም ስሮች፣ 60ሺህ
ቀለም አመንጪ ሴሎችና ከአንድ ሺህ በላይ የነርቭ ሴሎች ጫፍ አሉት፡፡
*************************************
ምንጭ :--http://www.addisadmassnews.com
Reader’s nigest - September 2013
By Dr. Traris Stork