ከደራሲያን ዓምባ

Saturday, November 24, 2012

አራምባና ቆቦ

ሁሉ አማረኝን - ወደ መድረክ አታውጣት።
ህልም ተፈርቶ - ፓርላማ አይታደርም።
ሆድ ለባሰው - ኬክ ጋብዘው።
ሆድ ለባሰው - የጤፍ ዋጋን ንገረው።
ሆድ ሲያውቅ - በሚሊንየም ስንቅ።
ሆድ ለባሰው - ሚጥሚጣ አቅምሰው።
ሃምሳ ሎሚ - ሊጀመር ነው።
ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ አሸባሪ አያስፈራትም።
   ልፋ ያለው - ሀውልት ያስመልሳል።
   ሌባ ላመሉ - ሙስና ኮሚሽን ያቋቁማል።
   ላም አለኝ በሰማይ - ስሞት እንገናኝ።
   ልጅ ለእናቷ - ልጅ ነች።
******************************
ምንጭ:--ቁም ነገር መጽሄት