ከደራሲያን ዓምባ

Wednesday, August 4, 2021

ኢትዮጵያና ኦሎምፒክ

 ኦሎምፒክና የኢትዮጵያ ወርቃማ ኦሎምፒያኖች_ግሩም ሠይፉ( አዲስ )

 


1896 እኤአ ላይ የግሪኳ አቴንስ ከተማ ካስተናገደችው የመጀመርያው ኦሎምፒድ አንስቶ ባለፉት 125 ዓመታት ውስጥ በተካሄዱት 31 ኦሎምፒያዶች ኢትዮጵያ 13 ተሳትፋለች፡፡ በኦሎምፒክ መድረክ ሁሉንም ሜዳልያዎችን የሰበሰበችው በአትሌቲክስ ስፖርት ብቻ ሲሆን በከፍተኛ የውጤት ታሪካቸው ከሚጠቀሱ 8 አገራት አንዷ ናት። አፍሪካን በመወከል ደግሞ ከኬንያ ቀጥሎ ከፍተኛውን ስኬት አስመዝግባለች፡፡
የጃፓኗ ቶኪዮ ከምታስተናግደው 2020 32ኛው ኦሎምፒያድ በፊት ኢትዮጵያ በተካፈለችባቸው 12 ኦሎምፒያዶች 227 ኦሎምፒያኖች (168 ወንድ እና 59 ሴትተሳትፈዋል፡፡ ከእነሱም መካከል 32 ኦሎምፒያኖች 1 እስከ 3 ባሉ ደረጃዎች ስኬታማ በመሆን 54 ሜዳልያዎችን (22 የወርቅ፤ 11 የብርና 21 የነሐስ) ለኢትዮጵያ አስገኝተዋል፡፡
ከሜዳልያዎቹ ስብስብ 22 የወርቅ ሜዳልያዎችን ለኢትዮጵያ ያጎናፀፉት 13 ኦሎምፒያኖች ናቸው፡፡ በተረፈ 11 የብር ሜዳልያዎች 10  እንዲሁም 21 የነሐስ ሜዳልያዎች 18 የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች ተገኝተዋል፡፡

የወርቅ ሜዳልያ ክብርና ዋጋ
ኦሎምፒክ የዓለም አገራትና ህዝቦቻቸውን በአንድ መንፈስ የሚያስተባብር መድረክ ነው፡፡ በስፖርት መድረኩ በድህነት የተጎሳቆሉ፤ በበቂ የስፖርት መሰረተ ልማት ዝግጅታቸውን ያላከናወኑ፤ በየአገራቸው ባሉ የፖለቲካ አለመረጋጋቶች የተረበሹ፤ በጦርነት እና በኢኮኖሚ ቀውስ የሚገኙ አገሮቻቸውን የወከሉ ኦሎምፒያኖች ሲሳተፉ ሁሉም አንድ ዓላማ ይኖራቸዋል፡፡ ይህ ዓላማ በሜዳልያ ክብር አገራቸውን ማኩራትና ሰንደቅ አለማቸውን ማውለብለብ ነው፡፡ የኦሎምፒክ የሜዳልያ ክብር መጎናፀፍ  ደግሞ የየትኛውም የዓለም ስፖርተኛ ህልም እንደሆነ ይታወቃል።
በኦሎምፒክ ታሪክ ሙሉ ለሙሉ ከወርቅ የተሰሩ ሜዳልያዎች ለአሸናፊዎች ለመጨረሻ ግዜ የተሰጠው 1912 እኤአ ላይ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ የኦሎምፒክ ሜዳልያዎች ገፅታ በአዘጋጅ አገራት የዲዛይን ፍላጎት እንዲሆን ቢፈቀድም ሜዳልያዎኙ የሚሰሩበት ማእድን በኦሎምፒክ ቻርተር መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡ በኦሎምፒክ 1 እና ሁለተኛ ደረጃ የሚሸለሙት የወርቅና የብር ሜዳልያዎች 92.5 በመቶ የሚሰሩት ከብር  እንዲሁም 6 በመቶ ከመዳብ ነው፡፡
3 ደረጃ ተሸላሚዎች የሚሰጡት የነሐስ ሜዳልያዎ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ከነሐስ የተሰሩ ናቸው፡፡ የወርቅ ሜዳሊያዎች 6 ግራም ወርቅ መለበጣቸው ግድ ነው፡፡ ሁሉም ሜዳልያዎች ውፍረታቸው 3ሚሜ  ዲያሜትራቸው 60 ሚሜ መሆን አለበት፡፡ አንድ የወርቅ ሜዳልያን አቅልጦ ይሸጥ ቢባል 706 ዶላር ጀምሮ ዋጋ ይኖረዋል፡፡
30ኛው ኦሎምፒያድ 4700 ሜዳልያዎች ለተሸላሚዎች የተዘጋጁ ሲሆን በሜዳልያዎቹ ስራ 802 ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡  ለኦሎምፒክ ሻምፒዮኖች የቀረቡ 302 የወርቅ ሜዳልያዎች 400 ግራም ይመዝናሉ፡፡


አበበ ቢቂላ
ትውልዱ ደብረብርሃን አቅራቢያ ጃቶ በተባለች ቦታ ነበር፡፡ 1960 እኤአ 83 አገራት የተውጣጡ 5 በላይ አትሌቶች በተካፈሉበት የሮም ኦሎምፒክ ላይ ለአፍሪካ እና ለኢትዮጰያ በኦሎምፒክ ታሪክ የመጀመርያውን ሜዳሊያ በማስገኘት ፈርቀዳጅ ታሪክ ሰርቷል፡፡  በባዶ እግሩ  ሮጦ ታላቁን የኦሎምፒክ ማራቶን በአንደኝነት ከማሸነፉም በተጨማሪ፤ 2162 በሆነ ሰአት አዲስ የአለም ሪከርድ አስመዝግቦም ነበር፡፡  
4 ዓመታት በኋላ 1964 እኤአ የኦሎምፒክ አዘጋጅ የጃፓኗ ከተማ ቶኪዮ ነበረች፡፡ የቶኪዮ ኦሎምፒክ 6 ሳምንታት ሲቀሩት፤ አበበ ቢቂላ የቀዶ ህክምና ተደርገለት። በፍጥነት እንደሚያገግም ተስፋ በማድረግ፤ የኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ መካተቱ አልቀረም፡፡
ከቀዶ ጥገናው ሙሉ ለሙሉ ሳያገግም ማራቶኑን በመሮጥ በድጋሚ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ሆኖ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ አስመዘገበ፡፡ ድሉ ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ ብቻ አልነበረም  በድጋሚ የዓለም  ማራቶንን ሪከርድ አሻሽሏል - 21211 በሆነ ሰአት በመግባት፡፡ በሁለት ኦሎምፒኮች  በማራቶን አከታትሎ  በማሸነፍ፤ በሁለቱም ሪከርድ በማስመዝገብ እና ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎች በማግኘት፤ አበበ ብቸኛው ኦሎምፒያን ነው፡፡

ማሞ ወልዴ
ማሞ ወልዴ የተወለደው ከአዲስ አበባ 60 .. ርቀት ድሪጂሌ በተባለች የገጠር ከተማ ተወልዷል፡፡ ከአበበ ቢቂላ በኋላ የኢትዮጵያ ብቸኛ ተስፋ አንተ ብቻ ነህ ተብሎ 1968 እኤአ ላይ የሜክሲኮን ኦሎምፒክ የተሳተፈ ነበር፡፡
በሜክሲኮ ኦሎምፒክ 10 ሜትር ውድድር ኢትዮጲያን ወክሎ እንዲሮጥ የተመረጠው አትሌት ማሞ፤ ከከባድ ተቀናቃኞች ጋር ተፎካክሮ በአጨራረስ ብልሃት ስላልነበረው  ውድድሩን በሁለተኛነት ጨርሶ፤ በኦሎምፒክ ተሳትፎው ለራሱ የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ ተጎናፅፏል፡፡
 ማሞ ወልዴ 10 ሜትር የብር ሜዳልያው ድል በኋላ ግን ከዚህ አድካሚ ውድድር እፎይ የሚልበት ጊዜ አልነበረውም፤ በማራቶን እንዲወዳደርና የአበበን የድል ታሪክ መድገም እንደሚኖርበት የኢትዮጲያን ክብር የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት በወቅቱ አሰልጣኝ የነበሩት አሰልጣኝ ንጉሴ ሮባ ተነገረው፡፡ 10 ሜትር ተወዳድሮ የብር ሜዳልያ ባገኘ በማግስቱ ነበር ማራቶኑ፡፡ ለመፎካከር ከተሰለፉት 44 አገራት አትሌቶች ውስጥ፤ ከኢትዮጲያ አበበ ቢቂላ፤ ማሞ ወልዴና ደሞሴ ነበሩበት፡፡ 15 ኪሎ ሜትር  ያህል  ሲመራ የቆየው የማራቶን ጀግና አበበ ቢቂላ በህመም ውድድሩን አቋርጦ ለመውጣት ተገደደ፡፡ የስፖርት አፍቃሪዎች ልብ በሃዘን ተሰበረ፡፡  ጀግና ጀግናን እንደሚተካ የተዘነጋ ይመስላል፡፡  
በአበበ ቢቂላ በተከታታይ ሁለት ኦሎምፒክ ድል የተገኘበትን የማራቶን ውድድር ማሞ ወልዴ በድጋሚ አሸንፎ ታሪክ በመስራት የኢትዮጵያን ክብር አስጠበቀ፡፡ 35 አመቱ በአንድ ኦሎምፒክ ሁለት ሜዳሊያ ያጠለቀው ማሞ፤ ጀግንነቱ ለኢትዮጵያውን ኩራትንና ደስታን አጎናፀፈ፡፡ ከዚህ ስኬቱ በኃላ አትሌት ማሞ ወልዴ 1965 በጀርመን ሙኒክ በተካሄደው ኦሎምፒክ 10 ሜትር ሶስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳሊያ አግኝቷል፡፡


ምሩፅ ይፍጠር
ምሩፅ ይፍጠር በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ውስጥ በአዲግራት ተወለደ፡፡ በወጣትነቱ ከጋሪ ነጂ ጀምሮ፤ በተለያዩ ፋብሪካዎች ተቀጥሮ ሰርቷል፡፡
ለመጀመርያ ጊዜ በኦሎምፒክ የተሳተፈው የጀርመኗ ከተማ ሙኒክ ባስተናገደችው ኦሎምፒክ ሲሆን በአስር ሜትር ሶስተኛ ወጥቶ የነሃስ ሜዳሊያ አግኝቷል፡፡በ1980 እኤአ የራሽያ ዋና ከተማ ያስተናገደችው የሞስኮ ኦሎምፒክ የምሩፅ ነበር፤ አለምን ጉድ ያሰኘበት፡፡ በሞስኮ ኦሎምፒክ 10ሺና 5 ሜትር ኢትዮጵያን በመወከል የተወዳደረው ምሩፅ፤  በፍፁም ብቃት በሁለቱም በማሸነፍ ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎችን ያገኘ ሲሆን በሁለቱም ርቀቶች በኦሎምፒክ ያሸነፈ የመጀመርያው አትሌት ነበር፡፡



ደራርቱ ቱሉ
ደራርቱ ቱሉ ትውልዷ በአርሲዋ ትንሽ ከተማ በቆጂ ነው፡፡  አትሌት ደራርቱ ቱሉ ለኢትዮጲያዊያን ብቻ ሳይሆነ ለአፍሪካዊያን እንስት አትሌቶች ፈርቀዳጅ የሆኑ ድሎችን በአለም አቀፍ ደረጃ ታሪክ ሠርታለች፡፡
በተለይ ደግሞ የሚጠቀሰው  1992 .. በስፔን ባርሴሎና በተከናወነው ኦሎምፒክ  10 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ መጎናፀፏ ነው፡፡ ይህ ድል በአፍሪካ የኦሎምፒክ ታሪክ በረጅም ርቀት በሴቶች የመጀመርያው ድል ነበር። 2000 እኤአ በአውስትራያ በተካሄደው የሲድኒ ኦሎምፒክም ደራርቱ 10 ሜትር ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ ለመጎናፀፍ በቅታለች፡፡ በተጨማሪም 2004 እኤአ በአቴንስ ኦሎምፒክ 10 ሜትር የነሐስ ሜዳልያ አግኝታለች፡፡

 




ፋጡማ ሮባ
አትሌት ፋጡማ ሮባ  የተወለደችው በአርሲዋ በቆጂ ከተማ ነው፡፡ 1996 .. ላይ የአሜሪካዋ አትላንታ ባስተናገደችው ኦሎምፒክ በሴቶች ማራቶን በታሪክ የመጀመርያውን የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮ ለመጎናፀፍ በቅታለች፡፡

 


 ኃይሌ ገብረስላሴ
ትውልዱ በአርሲዋ ትንሽ ከተማ በቆጂ ነው። ኃይሌ /ሥላሴ ለመጀመርያ ጊዜ 1996 .. ላይ በአትላንታ ኦሎምፒክ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በመሳተፍ 10 ሜትር ውድድር ተካፍሎ በአስደናቂ የአጨራረስ ብቃት በማሸነፍ የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አግኝቷል፡፡
2000 .. ላይ 20ኛው ክፍለ ዘመን የመጨረሻ ኦሎምፒክ በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ ሲካሄድ ኃይሌ 10 ሜትር በተካሄደው ውድድር  ከቅርብ ተቀናቃኙ የኬንያው አትሌት ፖልቴርጋት ጋር ያደረገው እልህ አጨራረስ ትንቅንቅ 0.09 ሰኮንድ ልዩነት በመቅደም 2ኛውን የወርቅ ሜዳልያ ለመጎናፀፍ በቅቷል፡፡

 


ሚሊዩን ወልዴ
አትሌት ሚሊዩን ወልዴ ትውልዱ በአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡ 2000 .. በአውሰትራሊያ ሲዲኒ በተከናውነው 27ኛው ኦሎምፒያድ አዲስ እና ፈርቀዳጅ ታሪክ ለኢትዮጰያ አትሌቲክስ በማስመዝገብ ተሳክቶለታል፡፡  
በወቅቱ 22 ዓመት ወጣት የነበረው አትሌት ሚልዩን በተካፈለበት 5 ሜትር ውድድር አሸንፎ በርቀቱ የመጀመርያውን የወርቅ ሜዳልያ ሲያስመዘግብ በመጨረሻዎቹ 200 ሜትሮች ድንቅ የአጨራረስ ብቃት በማሳየት  ነበር፡፡


ገዛሐኝ አበራ

የአትሌቶች መፍለቂያ በሆነችው አርሲ የተወለደው ገዛሐኝ በኢትዮጲያ የኦሎምፒክ ተሳትፎ ታሪክ ማሞ ወልዴ ካስመዘገበው የወርቅ ሜዳልያ በኋላ በማራቶን ሊያሽንፍ የበቃ አትሌት ነው፡፡
2000 እኤአ በሲዲኒ ኦሎምፒክ ላይ ገዛሐኝ በማራቶን የወርቅ ሜዳልያውን ሊጎናፀፍ የበቃ ሲሆን  22 ዓመቱ በኦሎምፒክ ታሪክ የመጀመሪያው ወጣት የማራቶን ባለድል ለመሆን ፈርቀዳጅ ታሪክ ለመስራት የቻለበት ነበር፡፡



ቀነኒሳ በቀለ
ትውልዱ በአርሲ በቆጂ የሆነው ቀነኒሳ 10 ሜትር ሶስት ጊዜ 5 ሜትር አንድ ጊዜ በአጠቃላይ 4 የኦሎምፒክ የወርቅ እንዲሁም በሺ ሜትር 1 የብር ሜዳልያዎችን በተጨማሪ በማስመዝገብ በወንድ አትሌቶች በኦሎምፒክ መድረክ ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበ ነው፡፡
ቀነኒሳ በኦሎምፒክ መድረክ የመጀመርያ ተሳትፎው 28ኛው ኦሎምፒያድ በግሪክ አቴንስ ላይ የነበረ ሲሆን፤  አዲስ የኦሎምፒክ ክብረወሰን በማስመዘገብ ለራሱ የመጀመርያውን የወርቅ ሜዳልያ ለማጥለቅ በቃ፡፡ በወንዶች 5 ሜትር ደግሞ የብር ሜዳልያ ነበረው፡፡
4 ዓመታት በኋላ የቻይናዋ ዋና ከተማ ባስተናገደችው 29ኛው ኦሎፒያድ በድጋሚ አዲስ የኦሎምፒክ ክብረወሰን በማስመዝገብ 10 ሜትር የሻምፒዮናነት ክብሩን አስጠብቆ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ ሊያገኝ የበቃ ሲሆን 5 ሜትርም ድል በማድረግ ሌላ የወርቅ ሜዳልያውንም ተጎናፅፏል፡፡ 1980 እኤአ ላይ በሞስኮ ኦሎምፒክ አትሌት ምሩፅ ይፍጠር  5ሺና 10 ድርብ ድል በማግኘት ያስመዘገበውን ታሪክ በመድገምም አስደናቂ ታሪክ ሊሰራ በቅቷል፡፡ 2012 እኤአ ለየእንግሊዟ ከተማ ለንደን ባስተናገደችው 30ኛው ኦሎምፒያድ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 10 ሜትር ለሶስትኛ ጊዜ የወርቅ ሜዳልያ በመጎናፀፍ በታሪክ የመጀመርያው አትሌት ሆኖ አዲስ ታሪክም ሊያስመዘግብ በቅቷል፡፡


ጥሩነሸ ዲባባ
ትውልዷ አርሲ ውስጥ በቆጂ አጠገብ በምትገኝ ጨፌ በተባለች ስፍራ ነው፡፡ ጥሩነሽ ዲባባ በኢትዮጲያ የኦሎምፒክ ተሳትፎ ታሪክ በሁለቱም ፆታዎች  እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛው የውጤት ክብረወሰን በማስመዝገብ በግንባርቀደምነት ትጠቀሳለች፡፡
ጥሩነሽ ዲባባ በተሳተፈችባቸውየኦሎምፒክ መድረኮች  2004 እኤአ በአቴንስ፤ 2008 እኤአ በቤጂንግ እንዲሁም 2012 እኤአ በለንደን 5 (3 የወርቅና ሁለት የነሐስ) ሜዳልያዎችን በማግኘት ከረጅም ርቀት አትሌቶች በአንደኛ ደረጃ የከፍተኛ ውጤት ክብረወሰን ይዛለች፡፡
እነዚህ ሜዳልያዎች ላይ 5 ሜትር ነሐስ 2004 አቴንስ ላይ፤  10 እና 5 ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎች 2008 ቤጂንግ ላይ፤ እንዲሁም  10 ወርቅ እና 5 ነሐስ ሜዳልያዎች 2012 ለንደን ላይ ያገኘቻቸው ናቸው።
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ደግሞ 5 የወርቅ እና ሜዳልያዎች በመሰብሰብ በረጅም ርቀት ብቸኛውን የውጤት ክብረወሰን እንደያዘች ነው፡፡

 


መሰረት ደፋር
አትሌት መሰረት ደፋር ትውልዷ በአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡ በኦሎምፒክ የተሳትፎ ታሪክ 5 ሜትር ሴቶች ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎችን ያስመዘገበች ምርጥ አትሌት ናት፡፡
የመጀመርያ የወርቅ ሜዳልያዋን ያስመዘገበችው 2004 እኤአ በአቴንስ ኦሎምፒክ ሲሆን በተመሳሳይ 5 ሜትር የነሐስ ሜዳልያ 2008 ቤጂንግ ላይ አስመዝግባ 2012 ለንደን ደግሞ በኦሎምፒክ የተሳትፎ ታሪኳ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ 5 ሜትር አስመዝግባለች፡፡


ቲኪ ገላና
30ኛው የለንደን ኦሎምፒያድ 2012 አትሌት ፋጡማ ሮባ 16 ዓመታት በፊት በአትላንታ ኦሎምፒክ ያስመዘገበችውን ታሪክ በመድገም ለሁለተኛ ጊዜ በሴቶች ሁለተኛውን የማራቶን የወርቅ ሜዳልያ የተጎናኘፈች ናት፡፡
በለንደን ኦሎምፒክ ቲኪ ገላና በማራቶን አሸንፋ የወርቅ ሜዳልያ የተጎናፀፈችው አዲስ የኦሎምፒክ ክብረወሰን በማስመዝገብ ጭምር ነው፡፡

 


አልማዝ አያና
ትውልዷ በቤንሻንጉል ጉምዝ ነው፡፡በብራዚል ሪዮ ዲጄኔሮ በተካሄደው 31ኛው ኦሎምፒያድ 10 ሜትር ብቸኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ወስዳለች፡፡ ያስመዘገበችው ሰዓት 2917.45 አዲስ የዓለም ሪከርድ ነው፡፡
23 ዓመታት በቻይናዊ አትሌት ተይዞ የነበረውን ሰዓት 14 ሰከንዶች ያሻሻለ ነው፡፡ በዚያው 31ኛው ኦሎምፒያድ ላይ   በተጨማሪ 5 ሜትር የነሐስ ሜዳልያ አግኝታለች፡፡



55 ሜዳልያዎች ከዓለም 41
በወንዶች
12 የወርቅ፣ 6 የብርና 12 የነሀስ ሜዳሊያዎች 4 ደረጃዎች 9 5 ደረጃዎች 3 እና 8 ደረጃዎች 30
1-5 ደረጃ ውጤች 30 ነጥብ - ከዓለም 17
በሴቶች
10 የወርቅ፣ 5 የብርና 9 የነሐስ ሜዳሊያዎች
4 ደረጃዎች 8 5 ደረጃዎች 5 6 ደረጃዎች 1 7 ደረጃዎች 3 እና 8 ደረጃዎች 2
1-3 ደረጃ ውጤቶች 24 ነጥብ - ከዓለም 11 55 የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ሜዳልያዎች 31 ኦሎምፒያዶች ተካሂደዋል፡፡ 

 ኢትዮጵያ 13 ተሳትፋለች 12 የወርቅ፣ 11 የብር እና 21 የነሐስ ሜዳሊያዎች፤  4 ደረጃዎች 17 5 ደረጃዎች 8 6 ደረጃዎች 11 7 ደረጃዎች 6 እና 8 ደረጃዎች


 
የኦሎምፒክ ሪከርዶች
በኦሎምፒክ መድረክ በወንዶች  5 ሜትር እና 10 ሜትር ሁለት ክብረወሰኖችን የያዘው  ቀነኒሳ በቀለ ነው፡፡ ቀነኒሳ በቀለ ሁለቱንም የኦሎምፒክ ክብረወሰኖች እኤአ 2008 በቤጂንግ በተካሄደው 29ኛው ኦሎምፒያድ ሲያስመዘገባቸው 5 ሜትር 12 ደቂቃ 57.82 ሰኮንዶች እንዲሁም 10 ሜትር 27 ደቂቃ 04.7 ሰኮንዶች የሰፈሩ ናቸው፡፡
ኬንያውያን 800 1500 3 መሰናክልና በማራቶን የተያዙ የኦሎምፒክ ሪከርዶችን በመቆናጠጥ የተሻለ ውክልና አላቸው፡፡ በኦሎምፒክ መድረክ በሴቶች ምድብ በተመዘገቡ ሪከርዶች ኢትዮጵያ በሁለት አትሌቶች ስትጠቀስ ኬንያ ግን አንድም አላስመዘገበችም፡፡
በኢትዮጵያውያን የተያዙት ሁለት የረጅም ርቀት የኦሎምፒክ ሪከርዶች 2016 እእአ ላይ በሪዩዲጄኔሮ ኦሎምፒክ አትሌት አልማዝ አያና 10 ሜትር  29 ደቂቃ 17.45 ሰኮንዶች በሆነ ጊዜ ያስመዘገበችውና 2012 እኤአ ላይ በለንደን በተካሄደው 30ኛው ኦሎምፒያድ ቲኪ ገላና በማራቶን ስታሸንፍ ርቀቱን የሸፈነችበት 2 ሰዓት 23 ደቂቃ 07 ሰኮንዶች፡፡

***   ***  ***  ***  ***  ***  ***  ***  ***  ***  ***  ***   ***  ***  ***  ***  ***  ***  ***
 

ንጭ :-- ኦሎምፒክና የኢትዮጵያ ወርቃማ ኦሎምፒያኖች - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news