ደራስያን በተለያዩ ዘመናትና ሁኔታዎች ውስጥ ያጋጠማቸውን የማኅበረሰቡን የሮሮም ሆነ የፍስሐ መንፈስ በመገምገምና
አስመስለው በመቅረጽ ሥነ ቃልን ይጠቀማሉ፡፡ ለመልዕክቶቻቸው ማጉያ በማድረግ በሚፈጥሯቸው ገፀ ባሕርያት አማካይነት
በልዩ ልዩ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸው ውስጥ ሲጠቅሷቸውም እናስተውላለን፡፡
"እግዚአብሔር ሲፈጥረኝ ጥንቱን በዚህ መሬት፣
ሳለቅስ ተወልጄ ሳለቅስ ኖሬበት፣
ሳለቅስ እንድሔድ ወደ ማልቀርበት፣
መከራን ጠግቤ ደስታን ምራብበት፣
ሌሎች የበሉትን እዳ ልከፍልበት፡፡ "
(ከ ፍቅር እስከ መቃብር)
it's right
ReplyDelete